Fana: At a Speed of Life!

የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሀም ከቱርክ አቻዎቻቸው ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ከቱርክ አቻቸው ጋር ተወያዩ።

ለቱርክ አፍሪክ አጋርነት ጉባዔ ኢስታንቡል የተገኙት ዶክተር አብርሃም፥ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከሀገሪቱ የመከላከያ ሚኒስትር ሁሉሲ አካር ጋር መወያየታቸውን ገልፀዋል።

ዶክተር አብርሃም በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳሉት “ከሰልጁክ ስረወ መንግስት እሰከ ኦቶማን ግዛታዊ መንግስትና የቅድመ ድንጋይ ዘመን ስልጣኔ ድረስ ስለሚዘረጋው የቱርክ ሪፐብሊክ ስልጣኔዎች በተለይም የመከላከያ ቴክኖሎጂ አስደማሚ እመርታን በሚመለከት ከወንድሜ ሁሉሲ አካር የቱርክ መከላከያ ሚኒስትር ጋር ያደረግኩት ውይይት ውጤታማ ነበር” ብለዋል።

አያይዘውም “ኢትዮዽያችን ዘመናት በሚሻገረው ስልጣኔዎችዋ መሰረትነት ተጠቅማ አዲሲቷ የተስፋ እድማስነት ከፍ ያለ ትልሟን በርግጥ ታሳካለች” ም ነው ያሉት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.