የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ አሸባሪው ህወሓት በሴቶች እና ህጻናት ላይ የፈጸመውን ጥቃትና አስገድዶ መድፈር የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ

By Feven Bishaw

December 19, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “እኔ የእህቴ ጠባቂ ነኝ፣ ሰላም ይስፈን፣ በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚደርስ ጥቃት ይቁም” በሚል መሪ ቃል አሸባሪው ህወሓት በሴቶች እና ህጻናት ላይ የፈጸመው ጥቃትና አስገድዶ መድፈር የሚያወግዝ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ ተካሄደ።

በሰልፉ ላይ “የአለም አቀፍ ሚዲያና የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የተዛባ ዘገባቸውን ያቁሙልን፣ በአፋርና አማራ ክልል በሴቶችና ህጻናት ላይ የደረሱ ጥቃቶች እና ጅምላ ጭፍጨፋ ፍትህ ይሻሉ”የሚሉ መልእክቶች ተላልፈዋል ።