Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ በአገር ውስጥ የማምረት አቅሟን ማሳደግና ዓለም ዓቀፍ የገበያ አማራጮቿን ማስፋት ይገባታል- የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ጫናውን ለመመከት በአገር ውስጥ የማምረት አቅሟን ማሳደግና ዓለም ዓቀፍ የገበያ አማራጮቿን ማስፋት እንደሚገባት የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ገለጹ።
በኢትዮጵያ ጦርነት ከፍቶ ዘርፈ ብዙ ጥፋት እያደረሰ የሚገኘውን አሸባሪው ህወሃትን የሚደግፉ አንዳንድ ምእራባውያን አገራት በአገሪቱ ላይ ጫና በማድረግ ኢኮኖሚ ለማዳከም እየሰሩ እንደሚገኙ ይታወቃል።
በኢኮኖሚው ላይ የተፈጠረውን ጫና ለመቋቋም በተለይ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ መተካት ላይ በትኩረት መሰራት እንዳለበት ኢዜአ ያነጋገራቸው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎች ጠቁመዋል።
ምርቶችን ከተለያዩ አገራት ለማስገባት የሚወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለመቀነስ የውጭ ምርትን በአገር ውስጥ መተካት እንደሚገባ ገልጸዋል።
የውጭ ምርትን በአገር ውስጥ የመተካት ጥረት አገሪቱ በምግብ ራሷን እንድትችል በማድረግ ረገድ ትልቅ ድርሻ እንዳለውም አብራርተዋል።
ኢትዮጵያውያን የአገር ወስጥ ምርቶችን የመጠቀም ባህላቸውን ማሳደግ እንደሚገባቸውም ጠቁመዋል።
የምጣኔ ሃብት ባለሙያው አቶ ደረጄ ደጀኔ አገሮች በኢኮኖሚ ማደግ የቻሉት የአገር ውስጥ የማምረት አቅምን በማሳደግ እንደሆነ ተናግረዋል።
ምርት ሲያድግ ከአገር ውስጥ ፍጆታ በላይ ለወጪ ንግድም ይተርፋል ነው ያሉት።
በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር ዶክተር ካሳ ተሻገር በበኩላቸው በአገር ውስጥ የሚመረቱ ምርቶችን ህብረተሰቡ እንዲጠቀማቸው ማድረግ ላይ መስራት እንደሚያስፈልግ ጠቁመዉ
ለአገር ውስጥ ምርት ያለው አመለካከት መሻሻልና መለወጥ እንዳለበትም ተናግረዋል።
ከውጭ የምናስገባቸውን ምርቶች አገር ውስጥ እንዲመረቱ ማበረታታት ያስፈልጋልያሉት ደግሞ በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ መምህር የሆኑት አቶ መዚድ ናስር ናቸው ።
የግል ዘርፉ ተሳትፎ እንዲያደርግና የምርት አቅርቦት የሚሻሻልበትን የፖሊሲ አማራጭ መፈተሽ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ኢትዮጵያ በዓለም ገበያ ልታቀርባቸው የምትችለው እና ያልተጠቀመችባቸው የግብርና እና ኢንዱስትሪ ውጤቶች አሏት፤በዚህም ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በማሳደግ በአውሮፓ፣ በእስያ እና በአፍሪካ አገራት ያሉ የገበያ አማራጮችን ማስፋት እንደሚገባም ነው የምጣኔ ሃብት ባለሙያዎቹ ያስገነዘቡት።
የግብርና መር ኢኮኖሚውን ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ስራዎችን በተጠናከረ ሁኔታ መስራት እንደሚገባም ተናግረዋል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.