Fana: At a Speed of Life!

በአሸባሪው ህወሓት የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የወገን አለኝታነቱን ማሳየቱን እንዲቀጥል ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 10፣2014(ኤፍ ቢሲ) በአሸባሪው ህወሓት የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የወገን አለኝታነቱን ማሳየቱን እንዲቀጥል የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ፡፡
 
በአሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የዱዓ እና የገቢ ማሰባሰቢያ የንቅናቄ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ ተካሂዷል።
 
በመድረኩ አሸባሪ ቡድኑ በአማራና በአፋር ክልሎች ንጹኃንን መግደሉ፤ ሴቶችን መድፈሩ፤ በርካታ ወገኖችንም ከመኖሪያ ቀያቸው ማፈናቀሉ ተመላክቷል፡፡
 
የእምነት ተቋማትን፣ ሕዝብ የሚጠቀምባቸውን መሰረተ ልማቶችን በማውደምና በመዝረፍ የሕዝብ ጠላትነቱን በተግባር አሳይቷል ነው የተባለው፡፡
 
የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሰኢድ መሀመድ አሸባሪው ህወሓት በወገኖቻችን ላይ ያደረሰው ግፍና መከራ ታሪክ ይቅር የማይለው አረመኔያዊ ድርጊት መሆኑን አንስተዋል፡፡
 
በቡድኑ የተጎዱ ወገኖችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋምም ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የድርሻውን መወጣቱን እንዲቀጥል ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
 
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር ድረስ ሳህሉ በበኩላቸው በሸብር ቡድኑ የተጎዳውን ኅብረተሰብ መልሶ በማቋቋም ከምንግዜውም በላይ ሁሉም እንዲረባረብ አሳስበዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.