Fana: At a Speed of Life!

የመዲናዋ አርሶ አደሮች ለመከላከያ ሰራዊት ከ11 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ነዋሪ የሆኑ አርሶ አደሮች ለአገር መከላከያ ሰራዊት ከ11ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።
 
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ አርሶ አደሮች በድል ላይ ድል እያስመዘገበ ላለው ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት 11 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር የሚገመት የአይነት ድጋፍ ይዘው ወደ ተለያዩ ግንባሮች ማቅናታቸውን በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡
 
የተደረገው ድጋፍ 135 ሰንጋዎች፣ 153 በግና ፍየሎችን ጨምሮ የተለያዩ የአይነት ድጋፎችን ያካተተ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
 
አርሶ አደሮቹ የዛሬውን የ11 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር ድጋፍ ሳይጨምር በተለያዩ ጊዜያት ከ 70 ሚሊየን ብር በላይ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ከንቲባዋ ጠቁመዋል፡፡
 
ከንቲባ አዳነች ለመላው የከተማመዋ አርሶ አደሮች ለዚህ ታላቅ ደጀንነት እና የአገር ፍቅር መገለጫ ለሆነው ተግባራቸው ትልቅ አክብሮት ያላቸውን መሆኑን ገልጸዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.