Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በወልዲያ ሆስፒታልና ዩኒቨርሲቲ ላይ ከፍተኛ ውድመት ፈጽሟል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 10፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ እና በወልዲያ አጠቃላይ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ላይ ከፍተኛ ዘረፋ እና ውድመት መፈጸሙ ተገለጸ፡፡
 
አሸባሪው ህወሓት የወልዲያ አጠቃላይ እስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን በመዝረፉና በማውደም በርካታ ሰዎች እንደስኳርና ደም ግፊት ባሉ በሽታዎች ህይወታቸው እንዲያልፍ ማድረጉ ተመላክቷል፡፡
 
የሽብር ቡድኑ የሆስፒታሉን ወሳኝ የህክምና ቁሳቁስ በህክምና ባለሙያ እየታገዘም ጭምር በመዝረፉ ከሆስፒታሉ አገልግሎት ያገኙ የነበሩ ዜጎችን ለከፋ ቀውስ መዳረጉ ነው የተገለጸው፡፡
 
ወራሪውና የሽብር ቡድኑ ህወሓት መድኃኒት ማከማቻና ለታካሚዎች አገልግሎት መስጫ ይውሉ የነበሩ መጋዘኖችን በመስበር መድኃኒቶችን ዘርፏል፤ አይጠቅሙኝም ያላቸውን ደግሞ በመሰባበር ከጥቅም ውጭ በማድረግ በመመስረቻ ሰነዱ ላይ ያሰፈረውን ጥላቻ በተግባር ገልጧል።
 
የወልዲያ አጠቃላይ እስፔሻላይዝ ሆስፒታል አሁን ባለበት ሁኔታ ምንም አገልግሎት መስጠት ስለማይችል የከተማው ማኅበረሰብ ከዚህ ለከፋ የጤና ቀውስ እንዳይዳረግ በተለይም የህክምና ክትትል ላይ ለነበሩ ወላዶች፣ ለህፃናት፣ ለስኳር፣ ደም ግፊትና የፀረ ኤች አይ ቪ ህክምና ተጠቃሚዎች በፍጥነት መድረስ እንዲቻል ጥሪ ቀርቧል።
 
በተመሳሳይ አሸባሪው ህወሓት የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ሁሉም ህንፃዎች ባሉ የመማሪያና አስተዳደር ክፍሎች የሚገኙ ሙሉ በሙሉ መዝረፉን ዋልታ ዘግቧል፡፡፡
 
በዩኒቨርሲቲው የሚተዳደረው 89 ነጥብ 2 ኤፍ ኤም የማኅበረሰብ ሬዲዮ ሙሉ እቃ ተጭኖ በሽብሩ ቡድኑ የተወሰደ ሲሆን፥ የዩኒቨርስቲው ሪጂስትራል ቢሮ ተሰብሮ የተማሪዎችን መረጃ የያዙ ካዘናዎችና ሙሉ ሰነዶች ከጥቅም ውጭ ሆነው መዝገቦች በየቦታው ተበታትነው ይታያሉ፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.