Fana: At a Speed of Life!

በወላይታ ሶዶና በዙሪያዋ ባሉ ከተሞች የኃይል መቆራረጥ ለመቀነስ የመካከለኛና ዝቅተኛ መስመር ማስፋፊያ ዝርጋታ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ሶዶና በዙሪያዋ ያሉ ከተሞችን የኃይል መቆራረጥ ለመቀነስ የሚያስችል የመካከለኛና የዝቅተኛ መስመር ማስፋፊያ ዝርጋታ ማከናወኑን የወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት ዲስትሪቡዩሽን ሜይቴናንስ ስራ አስኪያጅ ገረሱ ቴጋ አስታወቁ፡፡
በወላይታ ሶዶ፣ በዲሞቱ፣ በአርካ እና በዴሳ ከተሞች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ መገንባቱን የገለፁት አቶ ገረሱ÷ በዚህም 5 ነጥብ 99 ኪ.ሜ የዝቅተኛና 2 ነጥብ 3 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ፣ 7 አጋዥ ትራንስፎርመሮች በማስቀመጥ የኃይል መቆራረጥን መቀነስ ተችሏል ብለዋል፡፡
በማስፋፊያ ዝርጋታው ከ500 በላይ አዲስ ደንበኞች በማገናኘት የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ቡላባ ዳሮ ጡንቶ አዲሎ ከተማ 8 አዲስ ትራንስፎርመሮች መተከላቸውን የገለጹት ሥራ አስኪጁ÷ 14 ነጥብ 7 የዝቅተኛ መስመር ምሰሶ ቆሞ በመሰራት ላይ እንደሚገኝና በቅርቡ ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምርም አረጋግጠዋል፡፡
ዲስትሪክቱ በሚሸፍናቸው 14 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ላይ ከ50 በላይ ትራንስፎርመሮችን በመትከል የመልሶ ግንባታና አቅም ማሳደግ ስራዎች ለመስራት በዝግጅት ላይ መሆናቸውንም ተናግረዋል፡፡
የስድስቱ ከተማ የመልሶ ግንባታ አቅም ማሳደግ ፕሮጀክት ከሚከናወንባቸው ከተሞች ወላይታ ሶዶ ከተማ አንዷ መሆኗን የገለጹት ስራ አስኪያጁ፥ 59 ኪ.ሜ የዝቅተኛና 80 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር ዝርጋታ፣ 13 አዲስና 20 አጋዥ ትራንስፎርመር ማስቀመጥ መቻሉንም አንስተዋል፡፡
ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ገደብ አጠናቆ አስተማማኝኝ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ለከተማዋ ነዋሪዎች ለመስጠት እየተሰራ ነው መባሉን ከኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.