Fana: At a Speed of Life!

ሸኔ አባላት ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቄለም ወለጋ ዞን አንፍሎ እና ጋዎ ቄቤ ወረዳዎች የሸኔ አባላት ከዘረፉት ሀብት እና ከተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ከኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው÷ ቡድኑ ዘርፎት ከነበረው 56 ኩንታል ቡና እና 16 የተለያዩ ጠመንጃዎች ጋር ነው በቁጥጥር ስር የዋለው፡፡
በቁጥጥር ስር የዋሉት የሸኔ አባላት ቡድኑ ህብረተሰቡን በመዝረፍና በማሰቃየት ላይ እንደተሰማራ ገልጸው÷ በጫካ የቀሩት የቡድኑ አባላት እጅ እንዲሰጡ ጠይቀዋል፡፡
የአንፍሎ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ኃላፊ ሳጂን ተካልኝ ባሩ÷ በአካባቢው ዛላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማድረግ ህብረተሰቡ ከጸጥታ ኃይሎች ጋር የሚያደርጉትን ትብብር አጠናክሮ መቀጠል አለባቸው ብለዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.