Fana: At a Speed of Life!

ተላላክ፣ ደዌና ዳሊፋጌ ወረዳዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም አገኙ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ተላላክ፣ ደዌና ዳሊፋጌ ወረዳዎች ተቋርጦባቸው የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

አሸባሪው የህውሃት ቡድን በአፋር ክልል ወረራ ባደረገበት ወቅት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱ የሚታወስ ሲሆን፥ በዚህም ክልሉ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡

ሆኖም የአፋር ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ በአሁን ወቅት ተላላክ፣ ደዌና ዳሊፋጌ ወረዳዎች የኤሌክትሪክ ኃይል በድጋሚ ማግኘታቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በቀጣይም ቀሪ የጥገና ሥራዎች ተጠናቀው ሌሎች ከተሞችም የኤሌክትሪክ ኃይል እንደሚያገኙ የክልሉ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጿል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.