የሀገር ውስጥ ዜና

ተላላክ፣ ደዌና ዳሊፋጌ ወረዳዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም አገኙ

By Feven Bishaw

December 20, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ተላላክ፣ ደዌና ዳሊፋጌ ወረዳዎች ተቋርጦባቸው የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ዳግም ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

አሸባሪው የህውሃት ቡድን በአፋር ክልል ወረራ ባደረገበት ወቅት የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱ የሚታወስ ሲሆን፥ በዚህም ክልሉ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡