Fana: At a Speed of Life!

በ3ኛው የቱርክ አፍሪካ ጉባኤ አፍሪካውያን በራሳቸው መቆም እንዲችሉ ያለሙ ጉዳዮች በስፋት ተነስተዋል- የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በተሳተፈችበት በሶስተኛው የቱርክ አፍሪካ ጉባኤ አፍሪካውያን በራሳቸው መቆም እንዲችሉ የጋራ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮሩ ትብብሮች ያስፈልጓቸዋል የሚል ሀሳብ ተራምዶበታል፡፡
አፍሪካ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን ውክልና ማሳደግ እንደሚገባትና ዓለም አቀፍ መድረኮቹም በዛው ልክ ፍትሀዊ ሊሆኑ ይገባል የሚሉ ሀሳቦች በጉባኤው በስፋት መነሳታቸውን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ከዚህ ባለፈም በጉባኤው ኢትዮጵያ እና ቱርክ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን አጠናክረው በሚያስቀጥሉባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል ነው ያሉት፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተመራው ልዑክም በጉባኤው ስኬታማ ጊዜ ማሳለፉን ዴኤታዋ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት አሁንም የአሸባሪውን ቡድን በማስወገድ በኩል የተጠናከረ እርምጃዎችን በመውሰድ በርከት ያሉ ውጤቶች እየተገኙበት መሆኑን ሚኒስትር ዲኤታዋ አንስተዋል፡፡
በዚህም በአሸባሪው ቡድን ቁጥጥር ስር የነበሩ ብዙ ቦታዎች ነጻ መውጣታቸውን ጠቁመው÷ የሰሜን ወሎ ዞን ዋና ከተማ ወልዲያን ጨምሮ በወታደራዊም ሆነ በስትራቴጂካዊ ጠቀሜታቸው ከፍተኛ የሆኑ በርካታ ቦታዎች ነጻ መውጣታቸውን ቀጥለዋል ብለዋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት በገባባቸው አካባቢዎች ሁሉ ጥልቅ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ማድረሱንም ነው ሚኒስትር ዲኤታዋ የተናገሩት፡፡
በኢኮኖሚያዊ ዘርፉ ላይ በትኩረት እንደሚሠራ ገልጸው÷ በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ታሳቢ ባደረገ ሁኔታ በሌሎች አካባቢዎች በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ሥራ እየተሠራ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

 

በዮሐንስ ደርበው

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.