Fana: At a Speed of Life!

የዳላቲ-ኦዳ እና የጉባ ጎንቆሮ ቀበሌ የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ተቋርጦ የነበረው የዳላቲ – ኦዳ 40 ኪሎ ሜትር እና የጉባ ጎንቆሮ ቀበሌ የኤሌክትሪክ መስመር የጥገና ተጠናቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ እንዳመላከተው÷ ለረጅም ጊዜ ተቋርጦ የነበረው ከዳላቲ እስከ ኦዳ ያለውን እንዲሁም የጉባ ጎንቆሮ ቀበሌ የኤሌክትሪክ መስመር ሙሉ ጥገና በማጠናቀቅ ነው በአሁኑ ወቅት አገልግሎት እዲያገኙ የተደረገው፡፡
በዚህም ተበላሽተው የነበሩ 118 ኢንሱሌተር ሲኒዎች እና ተቆርጦ የነበረ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የዝቅተኛ መስመር ጥገና መከናወኑን የሪጅኑ ዲስትሪቢውሽን ጥገና ክፍል አስታውቋል፡፡
በተጨማሪም ከመንዲ እስከ ኦዳ 80 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ መስመር ውስጥ የገቡ ዛፎችን የማጽዳት እንዲሁም ወድቀው የነበሩ ሁለት ኮንክሪት ምሰሶዎችን በማንሳት አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ መደረጉ ተጠቁሟል፡፡
በተለያየ ምክንያት ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸው ስፍራዎችን የመጠገን ስራ እንደሚጀመር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መረጃ ያመላክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.