Fana: At a Speed of Life!

ድርቅን ለመቋቋም የውሃ መሰረተ ልማት ፕሮጀክትን ማስፋፋት ያስፈልጋል- የአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊዎች

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ድርቅን ለመቋቋም እና በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የወደሙ የውሃ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የውሃ መሰረተ ልማት ፕሮጀክትን ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ የአማራና የኦሮሚያ ክልል የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊዎች ገለጹ፡፡

የውሃ ማስተላለፊያ መስመሮችን፣ የውሃ ፓምፕ፣ ጀኔሬተር እና ቧንቧ ሳይቀር አሸባሪው ቡድን ዘርፎ መውሰዱን የገለጹት የአማራ ክልል የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው፥ ህብረተሰቡ የንጹህ መጠጥ ውሃ እንዳያገኝ፣ በውሃ ዕጦትና ጥም እንዲሰቃይ እኩይ ተግባር ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

የመጠጥ ውሃ ጥያቄ ጊዜ የማይሰጥ መሆኑን ያነሱት የኦሮሚያ ክልል የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር ሚሊዮን በቀለ በበኩላቸው፥ በአማራና አፋር ክልል የደረሰው ጉዳት ተጽዕኖ በኦሮሚያ ክልልም ደርሷል ብለዋል፡፡

የነፍስ አድን ስራዎችን ለመስራት ከዩኒሴፍ እና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት እየተሰራ እንደሚገኝ እና የተጀመሩ የውሃ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸውና በታቀደላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ሀላፊዋ ተናግረዋል፡፡

በርካታ የውሃ ተፋሰስ ወንዞች በኦሮሚያ ክልል እንደሚገኙ ጠቅሰው፥ ወንዞች ለመጠጥ ብቻ ሳይሆን ለመስኖ ስራም እንዲውሉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመጠገን የሚያገለግሉ መለዋወጫዎች ከውጭ የሚገቡ መሆናቸውን የገለጹት ሃላፊዎቹ፥ እነዚህ በመልሶ ግንባታው ሂደት እንደ ፈተና የሚገጥሙ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

በአማራ፣ አፋርና በሌሎች ክልሎች ያለው ችግር የኢትዮጵያ ችግር መሆኑን የጠቀሱት ሀላፊዎቹ፥ ጠንክረን መስራት ከቻልን በምግብ እራሳችንን መቻል እና ሀገራችንን ማሳደግ እንችላለን ብለዋል፡፡

ሃላፊዎቹ የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት እና ህብረተሰቡን ወደነበረበት ለመመለስ መንግስት ብቻ ሳይሆን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው ነው የተናገሩት፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.