የሀገር ውስጥ ዜና

ድርቅን ለመቋቋም የውሃ መሰረተ ልማት ፕሮጀክትን ማስፋፋት ያስፈልጋል- የአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊዎች

By Feven Bishaw

December 20, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ድርቅን ለመቋቋም እና በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የወደሙ የውሃ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የውሃ መሰረተ ልማት ፕሮጀክትን ማስፋፋት እንደሚያስፈልግ የአማራና የኦሮሚያ ክልል የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊዎች ገለጹ፡፡

የውሃ ማስተላለፊያ መስመሮችን፣ የውሃ ፓምፕ፣ ጀኔሬተር እና ቧንቧ ሳይቀር አሸባሪው ቡድን ዘርፎ መውሰዱን የገለጹት የአማራ ክልል የውሃ እና ኢነርጂ ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ማማሩ አያሌው፥ ህብረተሰቡ የንጹህ መጠጥ ውሃ እንዳያገኝ፣ በውሃ ዕጦትና ጥም እንዲሰቃይ እኩይ ተግባር ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል፡፡