Fana: At a Speed of Life!

ተቋሙ ከባለድርሻ አካላት ያሰባሰበውን 3 ሚሊየን ብር ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አብረውት ከሚሰሩት ባለድርሻ አካላት ያሰባሰበውን 3 ሚሊየን ብር በዛሬው ዕለት ለሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አስረክቧል፡፡
ድጋፉ የተደረገው በህልውና ዘመቻ ላይ መስዋዕትነት እየከፈለ ለሚገኘው ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ሲሆን፣ ከዚህ በፊት 4 ሚሊየን ብር ለአማራ ክልል መንግስት እንዲሁም 3 ሚሊየን ብር ለአፋር ክልል መንግስት ማስረከቡም ይታወቃል፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት ከተቋሙ ጋር አብረው የሚሰሩ ተቋራጮች፣ ግብዓት አምራቾችና ግብዓት አቅራቢዎች መሆናቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌሌክትሪክ አገልግሎት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሽፈራው ተሊላ፥ አሁናዊ የሃገራችን የፀጥታ ችግር በኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ተቋሙ ይህንን ጉዳት በአጭር ጊዜ ውስጥ ዕልባት ለመስጠት ከወራሪው ሃይል ነፃ የወጡ አካባቢዎችን እየተከታተለ ጥገና በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው፥ በቀጣይም የሃገራችንን ሁለተናዊ ልማት ለማስቀጠል ተቋሙ ከፍተኛ ርብርብ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት በኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር የፋይናንስና የስራ አመራር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሊዊጅ በበኩላቸው፥ ለተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው፤ ይህ አብሮነታችንን በማስቀጠል የጠላትን ክፋት መክተን የሃገራችን ኢትዮጵያን ከፍታ እናረጋግጣለን ብለዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.