Fana: At a Speed of Life!

ለወልዲያ ከተማና አካባቢው አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው የሀይል ማከፋፈያ ጣቢያ በህወሓት ተነቅሎ ተወስዷል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶሮ ግብር በተባለው ቦታ ለወልዲያ ከተማና አካባቢው አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው ባለ 230/33/15 ኪሎ ቮልት የሀይል ማከፋፈያ ጣቢያ በአሸባሪው ህወሓት ተነቅሎ ተወስዷል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የባለሙያዎች ቡድን በስፍራው ተገኝቶ እንዳረጋገጠው÷ ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያው ሙሉ በሙሉ በአሸባሪው ህወሓት ተነቃቅሎ ተወስዷል።
ማከፋፈያ ጣቢያው ከወልዲያ ነባር ባለ 66 ኪሎ ቮልት ማከፋፈያ ጣቢያ ጋር በመሆን ለወልዲያ ከተማ፣ ለወልዲያ ዪኒቨርሲቲ፣ ጭፍራ፣ ሲሪንቃ፣ ሳንቃ፣ ውርጌሳ፣ ውጫሌ፣ ጉባላፍቶ፣ ቃሊም፣ ጎብዬ፣ ሀራ፣ ሮቢት፣ ቆቦ፣ጊራና ከተሞች እና አካባቢያቸው የሚሄዱ መስመሮች ነበሩት።
የሽብር ቡድኑ ተንቀሳቃሽ ማከፋፈያ ጣቢያውን ጨምሮ ከነባሩ የወልዲያ ማከፋፈያ ጣቢያ የሥርጭት ትራንስፎርመሮችን ነቅሎ መውሰዱን እና የትራንስፎርመር ዘይት ገልብጦ መውሰዱን ማረጋገጥ መቻሉን ከኤሌክትሪክ ሀይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የዓይን እማኞቸ እንደገለፁት ሽብርተኛው ህወሓት የዘረፋ ቡድን ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የተዋቀረና ትራንስፎርመሩ ችግር አለበት ወይስ የለበትም የሚለውን እየተፈተሸ ነው የወሰደው።
በባለሙያዎች ቡድኑ የሚቀርበውን መነሻ መሰረት አድርጎ የጥገና ቡድኑ ከነሐሴ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የተቋረጠውን የወልዲያና አካባቢው ኤሌክትሪክ ለማገናኘት በፍጥነት የጥገና ሥራውን እንደሚጀምር ይጠበቃል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.