Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ-ቴሌኮም በ”ወደ ሀገር ቤት ጥሪ” ለሚመጡ እንግዶች 51 በመቶ ቅናሽ ሊያደርግ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ሀገር ቤት እንግባ ጥሪን ተቀብለው ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በአገልግሎቱ ላይ እስከ 51 በመቶ ቅናሽ ለማድረግ መዘጋጀቱን ኢትዮ-ቴሌኮም አስታወቀ።
ድርጅቱ በፌስቡክ ገጹ ባሰፈረው መልእክት÷ ወደ ሀገር ቤት ለመምጣት ለተዘጋጁ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በአገልግሎቱ ላይ እስከ 51 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን አስታውቋል።
ወደ አገር ቤት ለሚመጡ ከ1 ሚሊየን በላይ ዳያስፖራዎች አቀባበል ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አንስቶ በሆቴሎች፣ በትራንስፖርት አቅራቢዎች፣ በጉብኝት ስፍራዎች ለዚህ ክብረበዓል በተለየ ትኩረት እየተሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘም በከተማዋ የሚገኙ ሆቴሎች፣ የእንግዳ ማረፊያዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢዎች እስከ 30 በመቶ የዋጋ ቅናሽ ለማድረግ መዘጋጀታቸው ይታወቃል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.