Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በቆቦ ከተማ ከ120 በላይ ንጹሃንን በጅምላ ጨፍጭፏል፤ የ9 ወር ነፍሰጡርም ደፍሯል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በቆቦ ከተማ ከ120 በላይ ንጹሃንን በጅምላ መጨፍጨፉን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናገሩ።
አሸባሪው ህወሓት በወረራ ገብቶባቸው በነበሩ የአማራ እና አፋር ክልሎች የተለያዩ አካባቢዎች ንጹሃንን በጅምላ ከመግደል በተጨማሪ ከፍተኛ የንብረት ዘረፋና ውድመት መፈጸሙን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አሸባሪ ቡድኑ በቆቦ ከተማ በቆየባቸው ጊዜያት ንጹሃንን ያለ ርህራሄ ጨፍጭፏል፤ ነፍሰ ጡርን ጨምሮ በርካታ ሴቶችን መድፈሩንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
በሰው ልጅ ላይ ሊፈጸም የማይገባውን ግፍ እና መከራ በከተማው ነዋሪዎች ላይ መፈፀሙንም የአይን እማኞች ተናግረዋል።
አሸባሪ ቡድኑ በቆቦ ከተማ ከ120 በላይ ንጹሃንን በጅምላ በመጨፍጨፍ አረመኔነቱን በተግባር አሳይቷል ብለዋል።
ከዚህ በፊት አሸባሪ ቡድኑ በቆቦ ከተማ ላይ ከፍተኛ በደል ሲፈጽም መቆየቱን ያስታወሱት ነዋሪዎቹ፥ የዘጠኝ ወር ነፍሰ ጡርን ጨምሮ በርካታ ሴቶችን አስገድዶ መድፈርን ጨምሮ የጭካኔ በትሩን ማሳረፉን ጠቁመዋል።
ቡድኑ ወንዶች ላይ ከፍተኛ ድብደባ መፈጸሙን ጠቅሰው፥ የቡድኑ ታጣቂዎች ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ንብረት መዝረፍና ማውደምን ጨምሮ ያልፈጸሙት ግፍ እንደሌለም ነው የተናገሩት።
በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎችን በአደባባይ ያለ ርህራሄ በአሰቃቂ ሁኔታ መግደሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል።
በአሁኑ ወቅት ጥምር ጦሩ አሸባሪውን ቡድን በመደምሰስ አካባቢውን ከወራሪው ነጻ በማውጣቱ መደሰታቸውንም አስታውቀዋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.