Fana: At a Speed of Life!

ሽንፈት ተከናንቦ ወደ ትግራይ የሸሸው የህወሓት ወራሪ ኃይል የድል አድራጊ አቀባበል እንዲደረግለት ቢሞከርም ተቃውሞ እየገጠመው ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ግንባሮች ሽንፈት ተከናንቦ ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ ከሆነው የህወሓት ወራሪ ኃይል የተራረፈው ታጣቂ ወደ  ትግራይ ሲገባ የድል አድራጊ አቀባበል እንዲደረግለት ቢሞከርም ተቃውሞ እየገጠመው መሆኑን ታማኝ የመረጃ ምንጮቻችን ገልጸውልናል፡፡

እንደ መረጃ ምንጮቻችን ከሆነ፤ አሸባሪው ቡድን  የፈጸመው ወረራ ተቀልብሶ ክፉኛ ሽንፈት አጋጥሞት ወደ ትግራይ  ክልል እየገባ ነው፡፡

ሽንፈቱ ሊዋጥላቸው ያልቻለው የቡድኑ አመራሮች ወራሪ ኃይሉ ከፍተኛ ድል አስመዝግቦ  የመጣ በማስመሰል የድል አድራጊ አቀባበል እንዲደረግለት እየመከሩ ነው፡፡

ታጣቂዎች ወደ ከተማ ሲገቡ ጥይት ወደ ላይ በመተኮስ በከበሮና በጡሩንባ እንዲታጀቡ ጥረት ቢደረግም በርካታ ልጆቹን መስዋዕት ያደረገውና ወደ ‹‹አዲስ አበባ ለመግባት ጫፍ ደርሰናል›› በሚል የሀሰት ፕሮፕጋንዳ እየተጭበረበረ እንደነበር የተገነዘበው ህብረተሠብ አጋጣሚውን ተቃውሞውን ለመግለጽም እየተጠቀመበት ይገኛል፡፡

በድል እንደተመለሱ ለማስመሰል የሚሞክሩት የአሸባሪው ቡድን አመራሮች ሽንፈታቸውን ለማድበስበስ እንዲሁም አሁንም የሀሰት ዘመቻውን በማቀጣጠል ህብረተሠቡ ምንም መረጃ የለውም በሚል ንቀት ለተጨማሪ እኩይ አላማቸው ለማነሳሳት ‹‹ከፍተኛ ድል አስመዝግበናል። ጠላትን ስበን ወደምንፈልገው ቦታ ያመጣነው በመሆኑ አሁን ከመቼውም ጊዜ በላይ መስዋዕትነት የሚጠይቅ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡ የመጣውን ጠላት ለመደምሰስ ተጨማሪ ኃይል ስለሚያስፈልግ ሁሉም ትግራዋይ  የድሉ ተቋዳሽ  እንዲሆን  ወደ ግንባር መቀላቀል አለበት፡፡ ሁሉም  ሰው ያለውንም ሀብትና ጥሪት ለዘመቻው ማዋል ይጠበቅበታል›› በማለት ቅስቀሳ እያደረጉ መሆናቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠውልናል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.