የሀገር ውስጥ ዜና

ከሰሜን ኬንያ በመነሳት ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩ የሸኔ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Feven Bishaw

December 21, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከሰሜን ኬንያ በመነሳት ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት በመንቀሳቀስ ላይ የነበሩ የሸኔ የሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የሸኔ የሽብር ቡድን አባላቱ ከሰሜን ኬንያ በመነሳት ቦረና ዞንን አቋርጠውና ከህዝቡ ጋር በመመሳሰል ወደሀገር ቤት ለመግባት በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ ነው በመንግስት የፀጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር የዋሉት፡፡