ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ መቐለ 70 እንደርታ ሀዋሳ ከተማን አሸነፈ

By Tibebu Kebede

February 15, 2020

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 14ኛ ሳምንት ብቸኛ ጨዋታ ዛሬ ተካሂዷል።

ሀዋሳ ከተማን በትግራይ ስታዲየም ያስተናገደው መቐለ 70 እንደርታ 5 ለ1 በሆነ ሰፊ ልዩነት አሸንፏል።

የመቐለ 70 እንደርታን የማሸነፊያ ግቦች ኦኪኪ አፎላቢ፣ ሙሉጌታ ወልደጊዮርጊስ እና ቢያድግልኝ ኤልያስ አስቆጥረዋል።

የሀዋሳ ከተማን ብቸኛ የማስተዛዘኛ ግብ ደግሞ ብሩክ በየነ አስቆጥሯል።