Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በጎብዬ ከተማ ንጹሃን ዜጎችን በጅምላ መጨፍጨፉን ነዋሪዎች ተናገሩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በጎብዬ ከተማ ንጹሃንን በጅምላ ከመጨፍጨፍ ጀምሮ ነፍሰጡር እናቶችን ህክምና በመከልከል እንዲሞቱ እስከማድረግ የደረሰ ግፍ መፈጸሙን የከተማዋ ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡
 
አሸባሪው ህወሓት በአማራና አፋር ክልሎች በወረራ በያዘባቸው አካባቢዎች ንጹሃንን በጅምላ ከመግደል በተጨማሪ ከፍተኛ የንብረት ዘረፋና ወድመት ፈፅሟል።
 
የሽብር ቡድኑ በሌሎች አካባቢዎች የፈጸመውን ግፍ በጎብዬ ከተማም ደግሞታል፡፡
 
የአሸባሪ ቡድኑ ወራሪ ኃይሎች በከተማዋ ንጹሃንን በጅምላ ጨፍጭፈዋል፤ ሴቶችን አስገድደው ደፍረዋል፤ ንብረት ዘርፈዋል፤ መውሰድ ያልቻሉትን ደግሞ አውድመዋል፡፡
 
በተጨማሪም ነፍሰጡር እናቶች ህክምና እንዳያገኙ በመከልከል እናቶችን ጨምሮ ጨቅላ ህጻናት እንዲሞቱ ማድረጋቸውንም ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
 
በተመሳሳይ ነዋሪዎችን ህክምና በመከልከል በተለያዩ ተላላፊና ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች እንዲሞቱ ማድረጋቸውን ነው የገለጹት፡፡
 
የነዋሪዎችን ኪስ ከመፈተኝ ጀምሮ ከፍተኛ ዝርፊያ መፈጸማቸውን ጠቅሰው፤ በዚህም ለችግር መዳረጋቸውን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡
 
በዘመቻ ለህብረብሔራዊ አንድነት” የተሰማራው ጥምር ኃይል ከተማዋን ከአሸባሪ ቡድኑ ነጻ በማውጣቱ መደሰታቸውንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.