Fana: At a Speed of Life!

የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ክልል አቀፍ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በደቡብ ክልል በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
 
በደቡብ ክልል የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር ከ26 ሺህ በላይ አባዎራዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የደቡብ ክልል ሥራ ዕድል ፈጠራ ቢሮ ኃላፊ አቶ ቢራጋ ብርሃኑ ተናግረዋል።
 
በዚህ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር በሶዶ ከተማ ከ2 ሺህ 500 በላይ አባዎራዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ነው የተባለው።
 
እነዚህ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች በአከባቢ ጥበቃ፣ በጽዳትና ውበት፣ በደረቅ ቆሻሻ ማሰባሰብ፣በአነስተኛና መለስተኛ መሰረተ ልማት ዝርጋታ ማስፋፋት ዘርፍና በአረንጓዴ ልማት የተደራጁ ናቸው ተብሏል።
 
በዓለም ባንክ የሚደገፈው የምግብ ዋስትና መርሃ ግብር በክልሉ ተግባራዊ በተደረገባቸው አካባቢዎች በርካታ ዜጎችን ከድህነት በማውጣት ራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና መጫወቱ ተመላክቷል፡፡
 
የፕሮግራሙ ተጠቃሚ ዜጎች 26 ሺህ 076 ወይም በቤተሰብ ደረጃ 7 ሺህ 661 መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፥ ከእነዚህ መካከል 16 በመቶዎቹ ቀጥታ የሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች ናቸው ተብሏል፡፡
 
በማስተዋል አሰፋ

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.