Fana: At a Speed of Life!

ቆንስል ጀኔራል ዳኛቸው ይትባረክ ከፑንትላንድ ሶማሊያ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋሮዌ ፑንትላንድ ሶማሊያ የኢትዮጵያ ቆንስል ጀኔራል ዳኛቸው ይትባረክ ከፑንትላንድ ሶማሊያ የአገር ውስጥ ሚኒስትር መሐመድ አብዱረሺድ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በኢትዮጵያና በፑንትላንድ ሶማሊያ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
 
ሚኒስትር መሐመድ አብዱረሺድ በፑንትላንድ ሶማሊያ እና በኢትዮጵያ መካከል መልካም ትብብር መኖሩን ነው የገለጹት፡፡
 
ኢትዮጵያ በተለይ ለፑንትላንድ ሶማሊያ ወጣት ትምህርት ፈላጊዎች ነጻ የትምህርት እድል በመስጠት በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ለምታደርገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
 
በዘርፉ ያለው ድጋፍ የፑንትላንድ ሶማሊያን ተቋማት በማገዝና ውጤታማ በማድረግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡
 
ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በሌሎች ዘርፎችም ለፑንትላንድ ሶማሊያ ለምታደርገው ድጋፍም ምስጋና ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.