Fana: At a Speed of Life!

በቤልጂዬም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለተፈናቃዮች ከ221 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልጂዬም አንቶርፐን ከተማ የሚኖሩ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያን ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ221 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡
 
በቤልጂዬም አንቶርፐን ከተማ የሚኖሩ የኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያን ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት በጦርነቱ የተጎዱ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ የኮሚኒቲው ተወካይ በሆኑት አቶ አብነት አክሊሉ አማካኝነት ከ221 ሺህ ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል።
 
ገንዘቡን የተቀበሉት በብራስልስ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሂሩት ዘመነ ÷በአንቶርፐን የሚገኙ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና ማቅረባቸውን በብራሰልስ ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.