የሀገር ውስጥ ዜና

አየር መንገዱ “ለ1ሚሊየን ወደ ሃገር ቤት” ጥሪ ለሚገቡ ኢትዮጵያውያን ያደረገውን የዋጋ ቅናሽ ለተጨማሪ ቀናት አራዘመ

By Feven Bishaw

December 21, 2021

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለታላቁ ወደሃገር ቤት ጥሪ ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያደረገውን የዋጋ ቅናሽ ለተጨማሪ ጊዜ ማራዘሙን አስታወቀ።

አየር መንገዱ በትዊተር ገጹ ባሰፈረው ፅሁፍ “ለ1ሚሊየን ወደ ሃገር ቤት” ጥሪ ለሚገቡ ኢትዮጵያውያን ያደረገውን የትኬት ዋጋ ቅናሽ ለተጨማሪ ቀናት ማራዘሙን አስታውቋል።