Fana: At a Speed of Life!

በአውሮፓ ለተፈጠረው ውጥረት ተጠያቂው አሜሪካ ነች -ፑቲን

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 12 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአውሮፓ ለተፈጠረው ውጥረት መባባስ ዋና ተጠያቂዋ አሜሪካናት አሉ፡፡

ፑቲን ለአገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ ባለስልጣናት ባደረጉት ንግግር፥ ሩሲያ ለማንኛውም የምዕራቡ ዓለም ጥቃት በቂ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ናት ብለዋል፡፡

በየትኛውም ሃገር ትንኮሳ ከተፈጸመ በማንኛውም ጊዜ ሩሲያ የአጸፋ እርምጃ ትወስዳለች፤ ይህንን ለማድረግ ሙሉ መብት እንዳለን ሊታወቅ ይገባል ነው ያሉት፡፡

ፑቲን የሰሜን ጦር ቃል ኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በዩክሬን ከሚያደርገው ወታደራዊ እንቅስቃሴና በአካባቢው እያደረገ ለለው መስፋፋት መፍትሄ እንዲበጅለት ጠይቀዋል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌይ ሾይጉ በበኩላቸው፥ አሜሪካ ወደ 8 ሺህ የሚጠጉ ወታደሮችን በሩሲያ ድንበር አቅራቢያ ማስፈሯን ጠቅሰዋል።

ከዚህ ባለፈም ከኔቶ አጋር አካላት ጋር በተደረሰ ስምምነት ለሩሲያ ቅርብ በሆኑ አካባቢዎች የጦር ጄቶች ሲበሩ ተስተውለዋልም ነው ያሉት።

አያይዘውም የዩክሬን ጦር በኔቶ ህብረት ውስጥ እንዲሳተፍ የሚደረገው ሙከራ የደህንነት ስጋት መፍጠሩንም አስረድተዋል።

ቀደም ሲል አንድ ከፍተኛ የሩሲያ ዲፕሎማት ሩሲያ በምትፈልገው የደህንነት ዋስትና ጉዳይ ላይ በሞስኮ እና በዋሺንግተን መካከል ግንኙነት መጀመሩን እና ሁለቱ ወገኖች መግባባት ላይ ሊደርሱ እንደሚችሉ መናገራቸውን ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አስታውሷል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.