Fana: At a Speed of Life!

የህዝብ እና የሀገርን አደራ ለመወጣት ምንጊዜም ዝግጁ ነን- የሰሜን ምዕራብ ዕዝ የጦር አመራሮችና አባላት

 

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የህዝብ እና የሀገርን አደራ በማንኛውም ጊዜ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን የሰሜን ምዕራብ ዕዝ የጦር አመራሮች እና አባላት ተናገሩ።

የህወሓት የሽብር ቡድንን ለማጥፋት ከሜካናይዝድ እስከ አግረኛ ድረስ በመቀናጀት የተሰጠንን ግዳጅ በሚገባ ተወጥተናል አሁንም ለሃገራችን እንድነት እና ለዜጎች ሰላም ሃገር እና ህዝብ የሰጠንን አደራ በማንኛውም ጊዜ ለመወጣት ዝግጁ ነን ሲሉ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው የእዙ የጦር አመራሮችና አባላት ተናግረዋል።

ከነሃሴ ወር መጀመሪያ አንስቶ ከጋሳይ እስከ ድልብ ድረስ በነበረው ግዳጅ በሽብር ቡድኑ ላይ በተወሰደው የማያዳግም አርምጃ በርካታ አኩሪ ድሎች ተመዝግበዋል።

ከጉና፣ ጨጨሆ ፣ ደብረ ዘቢጥ፣ የጋሸና ዓፄ ውሃ እና የሃሙሲት የኮንክሪት ምሽጎችን ለመስበር ዕዙ በተለይም የ34ኛ (ግድግዳው) እና የ51ኛ ክፍለ ጦር የፈፀሙት ጀግንነት በታሪክ ይዘከራል ያሉት የሰሜን ምዕራብ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ጌታቸው ጉዲና ናቸው።

በጋሸና ግንባር ጠላት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ተዋጊዎችን አሰልፎ ለመዋጋት ቢሞክርም በቀላል መሰዋትነት አከርካሪውን ተመቶ ሙት እና ቁስለኛ ሆኖ የተረፈው ፈርጥጧል ብለዋል።

አሁንም በኀብረ ብሔራዊ አንድነት የኢትዮጵያን ሰላም ለማስጠበቅ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

 

በምንይችል አዘዘው

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.