Fana: At a Speed of Life!

በሀገር ግንባታ የምሁራን ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ ክልላዊ የምክክር መድረክ በወራቤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር ግንባታ ላይ የምሁራንን ሚና ማጎልበት ላይ ትኩረት ያደረገ ክልላዊ የምክክር መድረክ በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

የደቡብ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ከምሁራን ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው፡፡

በውይይቱ የበደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳን ጨምሮ ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች የተገኙ ሲሆን፥ “ዘላቂ ሰላም፣ ለፈጣን ልማትና ለስኬታማ ሀገረ መንግስት ግንባታ” በሚል መሪ ሀሳብ ከሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የተወከሉ ምሁራን እየተሳተፉ ነው።

መድረኩ በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች እንዲሁም በሀገር ግንባታ ላይ የምሁራን ሚናን ማጎልበት ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.