Fana: At a Speed of Life!

ቻይና የአውሮፓ ህብረት በሆንግ ኮንግ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ እየገባ ነው ስትል ከሰሰች

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህብረቱ የቻይና መልዕክተኛ ቢሮ እንዳስታወቀው የቻይና ራስ ገዝ በሆነችው ሆንግ ኮንግ እሁድ በተካሄደው የልዩ አስተዳደር ክልል ምርጫን በተመለከተ የአውሮፓ ህብረት ጣልቃ ገብቷል ሲል ከሷል፡፡

ቻይና ተቃውሞ ያቀረበችው የአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ እና የደህንነት ፖሊሲ ከፍተኛ ተወካይ ጆሴፕ ቦረል የሆንግ ኮንግ ሰባተኛ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ምርጫን አስመልክቶ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ነው።

በሆንግ ኮንግ ልዩ የአስተዳደር ክልል ህገ-መንግስት መሰረት ቻይና የራስ ገዝ አስተዳደሯን ደህንነት ለመጠበቅ ስትል ህጉን ተቀብላ ተግባራዊ አድርጋለች፤ የምርጫ ስርዓቱን አሻሽላለች ነው ያለው ቢሮው።

ምርጫው በሰላምና በስርዓት መካሄዱን የገለፁት ቃል አቀባዩ፥ የምርጫው ሂደት ፍትሃዊ፣ ግልጽ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የመራጮች ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ የተከበሩበት እንደነበረም አስታውቋል።

በቻይና የውስጥ ጉዳይ በሆነው የሆንግ ኮንግ ምርጫ ጣልቃ መግባት የሀገርን ሉኣላዊነት መዳፈር ነው ብሏል፡፡

ህብረቱ አለም አቀፍ ግንኙነቶች የሚገዙባቸውን መሰረታዊ ደንቦችን እንዲያከብር እና በሆንግ ኮንግ ጉዳዮች እና በቻይና የውስጥ ጉዳይ በማንኛውም መልኩ ጣልቃ መግባቱን እንዲያቆም እና የሆንግ ኮንግ ብልጽግናን እና መረጋጋትን ማደናቀፍ እንዲያቆም እናሳስባለን ማለቱን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.