Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ እንዲደረግ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸውም አሁን በሀገሪቱ የተከሰተው ጦርነት እንዳይከሰት የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች ብዙ መልፋታቸውን አስታውሰዋል፡፡
በጦርነቱም የሰው ልጅ ህይወት ጠፍቷል፤ ብዙዎቹም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል ብለዋል፡፡ የሃይማኖት ተቋማት እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መውደማቸውንም በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
ለተፈናቀሉ ወገኖች ኢትዮጵያውያን የቻሉትን ድጋፍ ማድረጋቸውን ጠቅሰው፥ ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
አሁን አገር እያስመዘገበችው ያለውን ድል በመጥቀስም ይህ ድል በተገኘባቸው አካባቢዎች ሁሉ የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ መኖሪያ አካባቢያቸው ስለሚመለሱ ዘላቂ መቋቋሚያ ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡
ለዚህም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኮሚቴ አቋቁሞ የጉዳቱን መጠን የመለየት ሥራ እየሠራ መሆኑን የጠቆሙት ተቀዳሚ ሙፍቲ፥ የባንክ ሂሳብ የተከፈተ በመሆኑ ኢትዮጵያውያን እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ድጋፉ በአማራ እና አፋር ክልሎች እንዲሁም ከወለጋ አካባቢ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚውል ነው ፡፡
የሃይማኖት አባቶች እና የሀገር ሽማግሌዎች የሰላምን መንገድ እንዲያሳዩ ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር እድሪስ በመግለጫቸው አሳስበዋል፡፡
በፈቲያ አብደላ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.