Fana: At a Speed of Life!

የድሬዳዋ አስተዳደርና ህዝብ ለተፈናቀሉ ወገኖች የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ አስተዳደርና ህዝብ በአማራ ክልል በአሸባሪው ህወሓት ለተፈናቀሉ ወገኖች በጥሬ ገንዘብና በአይነት የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃርን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች፣ አባ ገዳዎችና ኡጋዞች በባህር ዳር ተገኝተው ድጋፉን ለክልሉ አስረክበዋል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ ድጋፉን ላደረጉት የድሬዳዋ አስተዳደርና ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል።
አሸባሪው ህወሓት በክልሉ ወረራ በፈፀመባቸው አካባቢዎች ንብረት ከመዝረፍና ከማውደም ባለፈ በዜጎች ላይ ኢ-ሰብአዊ ድርጊት መፈጸሙን ተናግረዋል።
ያጋጠመውን ችግር በመተጋገዝና በመተባበር ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሁሉን አቀፍ ርብርብ እያደረጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የተፈናቀሉ ወገኖችን በማቋቋም ወደ ቀደመው ሰላማዊ ኑሯቸው እንዲመለሱ ለማድረግ እንዲሁም የወደሙ የመንግስትና የግል ተቋማትን መልሶ ለመገንባት መላ ኢትዮጵያውያን እያበረከቱ ያለውን አድተዋፅኦ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በበኩላቸው፥ በአሸባሪው ህወሓት አማካኝነት በክልሉ የደረሰው ጉዳት የድሬዳዋ አስተዳደርና ህዝብ ጉዳት መሆኑን ተናግረዋል።
በመሆኑም ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች የድሬዳዋ አስተዳደርና ህዝብ በጥሬ ገንዘብ 5 ሚሊየን እና 10 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የምግብና አልባሳት ድጋፍ ማድረጉን አመልክተዋል።
በአሸባሪው ህወሓት የተጎዱ ወገኖችን ለማቋቋም በሚደረገው ሁሉን አቀፍ ጥረት የአስተዳደሩና የህዝቡ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.