Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት ሳምንታት በተካሄደው “ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” የወገን ጦር በአሸባሪው ህወሃት ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሷል – የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ሳምንታት በተካሄደው “ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የሚመራው ጥምር የወገን ጦር በአሸባሪው ህወሃት ላይ በወሰደው እርምጃ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ መድረሱን የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት አስታወቀ፡፡

የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒሰትር ዲኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸው ባለፉት ሳምንታት በተካሄደው “ዘመቻ ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት” የወገን ጦር በአሸባሪው ህወሃት ላይ በወሰደው ርምጃ ቡድኑ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሷል ብለዋል፡፡

ኪሳራውም በተለይም በርካታ የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች እንዲደመሰሱ እና ከፊሉ ምርኮኛ እና ቁስለኛ እንዲሆኑ አድርጓል ነው ያሉት፡፡

አዲስ አበባ ልገባ ትንሽ ርቀት ቀርቶኛል እያለ ሲፎክር የነበረው ቡድኑም ተገዶ ወደ መጣበት ተመልሷልብለዋል በመግለጫቸው፡፡

 

ይህን ሽንፈቱን ለመደበቅም ብዙ ርቀት ሂዷል ያሉት ሚኒስትር ዴኢታው በተለይም የሽብር ቡዱኑ “ታጣቂዎቻችንን ከአማራ እና ከአፋር ክልል እንዲወጡ አድርገናል” የሚል ትርክት እያራገበ ነው ብለዋል፡፡

የውሸት ትርክቱም የዓለምን ህዝብ ለማሳሳት፣ የትግራይ ህዝብን ለማታለልና ልጆቹን ለተጨማሪ ጦርነት እንዲያዘጋጁ ለማድረግ የተደረገ ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜም የሽብር ቡድኑ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ከአማራና አፋር ክልሎች እየፈረጠጠ ነው ብለዋል አቶ ከበደ፡፡

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊቱም የሽብር ቡድኑ ዳግም ለኢትዮጵያ አንድነትና ሉዓላዊነት ስጋት እንዳይሆን አስፈላጊውን ርምጃ መውሰዱን ይቀጥላል ነው ያሉት፡፡

አንዳንድ የውጭ መገናኛ ብዙሃን “ለሰላም ብሎ ስልታዊ ማፈግፈግ አድርጓል” ብሎ የዘገቡት ዘገባ እየሞተ ያለውን ህወሓት ለማዳን እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ መሆኑንም ሚኒስቴር ዴኤታው ተናግረዋል።
በፌቨን ቢሻው

 

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.