የሀገር ውስጥ ዜና

ባለሃብቱ አቶ ሰይድ ዳምጠው የመቶ አለቃ ጌታቸው ሞሮዳን ልጅ ለማሳደግ ቃል ገቡ

By Feven Bishaw

December 22, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለሃብቱ አቶ ሰይድ ዳምጠው የሀገርን ህልውና በማስከበር ዘመቻው መስዋዕት የሆነውን የመቶ አለቃ ጌታቸው ሞሮዳን ልጅ (ቢኒያም ጌታቸውን) ለመደገፍ 500 ሺህ ብር በመለገስ በኦሮሞ የገዳ ስርዓት መሰረት ልጃቸው አድርገው ለማሳደግ ቃል ገብተዋል፡፡

ይህ ስነ-ስርአት አዲስ አበባ በሚገኘው የኦቢኤን ስቱዲዮ የተከናወነ ሲሆን÷ የኦቢኤን ማኔጅመንት በበኩሉ ለታዳጊው የ200 ሺህ ብር ድጋፍ ማበርከቱን የኦቢኤን ዋና ዳይሬክተር ጋዜጠኛ ዝናቡ አስራት ገልፀዋል።