Fana: At a Speed of Life!

የትህነግ የሽብር ቡድን በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በ180 ትምህርት ቤቶች ላይ ዘረፉና ውድመት ፈጽሟል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትህነግ የሽብር ቡድን ወረራ ፈጽሞባቸው በነበሩ አካባቢዎች ከ150 ሺህ ተማሪ በላይ የሚያስተናግዱ 180 ትምህርት ቤቶች ላይ ዘረፉና ውድመት መፈጸሙን የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ ገለጸ።
የመምሪያው ኃላፊ አቶ በድሉ ውብሸት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት የሽብር ቡድኑ ወሯቸው በነበሩ ወረዳዎች በ180 ትምህርት ቤቶች ላይ ዘረፋና ውድመት ፈጽሟል።
የቅድመ መደበኛና የልዩ ፍላጎት ተማሪዎችን ጨምሮ ከ150 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ያስተምሩ በነበሩ ትምህርት ቤቶች ላይ ጉዳት አድርሷል ያሉት የመምሪያ ሀላፊው፥ ሙሉ የመማሪያ ክፍልን ከማውደም ጀምሮ ፕላዝማዎችን፣ ቤተ ሙከራዎች፣ ቤተ-መጽሃፍቶችና ልዩ ልዩ የትምህርት መሳሪያዎች ላይ ዘረፋና ውድመት ማድረሱን ገልጸዋል።
እስካሁን በተሰበሰበ መረጃ ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለው ሀብት ዘረፋና ውድመት ደርሶበታል ያሉት የመምሪያ ሀላፊው ተቋማቱን መልሶ በማቋቋም ስራ ለማስጀመር እየሰራን ነው ብለዋል።
የሽብር ቡድኑ በፈጸመው ወረራ ምክንያት ትምህርት መስተጓጎሉን ጠቅሰው፥ በቀጥታና በተዘዋዋሪ በ14 ወረዳዎች በሚገኙ በ752 ትምህርት ቤቶች ለ1 ወር ያህል ትምህርት ተቋርጦ እንደነበር አስታውሰዋል።
አሁን ላይ የከፋ ጉዳት ከደረሰባቸው ጥቂት ትምህርት ቤቶች ውጪ የመማር ማስተማር ስራው እየተጀመረ ይገኛልም ነው ያሉት።
በግርማ ነሲቡ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.