Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል ከኢትዮጵያ ጂኦስፓሻል ኢንስቲቲዩት የቱሪስት ካርታ ተረከበ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ጂኦስፓሻል ኢንስቲቲዩት ያዘጋጀውን የቱሪስት ካርታ ለኦሮሚያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ አስረከበ፡፡
ለኢኮኖሚው ዘርፍ የዲጂታል አሰራር ትልቅ አስተዋፅኦ ያለው መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ካርታው የሀገር ውስጥና የውጪ ጎብኚዎች በኦሮሚያ ክልል ያለውን የቱሪዝም ሀብት በቀላሉ መረዳት እንዲቻል ተደርጎ የተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ጂኦስፓሻል ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቱሉ በሻ ተናግረዋል።
አሁን የተዘጋጀው ካርታ በየጊዜው እየዳበረ ለሁሉም ዜጎች በሞባይል መተግበሪያ ተደራሽ ለማድረግ እንደሚሰራም ገልፀዋል።
አሁን የተዘጋጀው የቱሪስት ካርታ በቢሮው ድረገጽ አማካኝነት መመልክት እንደሚቻል ተብራርቷል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ሰዓዳ ኡስማን በበኩላቸው÷ የቱሪስት ካርታ ዝግጅቱ በኦሮሚያ ክልል ያለውን እምቅ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የቱሪዝም ሀብቶች በአግባቡ ማወቅና በማስተዋወቅ ረገድ ትልቅ አበርክቶ ይኖረዋል ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል በቀጣይ አስር አመታት 25 የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማልማት እቅድ መያዙን የገለፁት የቢሮ ሀላፊዋ የሚሰራው በቴክኖሎጂ የታገዘ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከኦቢኤን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.