Fana: At a Speed of Life!

በጦርነቱ አሸናፊ ያደረገን አንድነታችን በመልሶ ማቋቋም ጊዜም መቀጠል አለበት – የክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊዎች

 

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነቱ አሸናፊ ያደረገን አንድነታችን በአሸባሪ ቡድኑ የወደሙ ተቋማቶች እና መሰረተልማቶቻችን መልሶ በመገንባትና የተፈናቀሉ ወገኖቻችን መልሶ ማቋቋም ስራ ላይም ተጠናክሮ ሊቀጥል እደሚገባ የአማራ እና የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊዎች ገለጹ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ሰዓዳ ዑስማን እና የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ጣሂር ሙሃመድ ከፋና ቲቪ ጋር ቆይታ አድርገዋል፡፡

የጦርነት ጥሩ ነገር አለው ባይባልም ከዚህ ጦርነት የኢትዮጵያውያን ልዩነታቸውን ወደጎን በመተው ከጫፍ ጫፍ አንድ ሆነው እንዲነሱ እና በጋራ አሸባሪዎችን መውጋታቸው ታሪካዊ ክስተት ሆኗል ያሉት የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ጣሂር ሙሃመድ ይህ አንድነታችን በቀጣይ በምንሰራቸው መልሶ የመገንባት እና መልሶ የማቋቋም ስራዎች በጋራ ልንደግመው ይገባል ብለዋል፡፡

ይህ ሲሆን ጠላቶቻችን ለአመታት እርስ በእርስ እንድንባላ የሰሩትን ሴራ አክሽፈን አዲስ የአብሮነት ታሪክ እንገነባለን ነው ያሉት፡፡

አሸባሪ ቡድኑ በአማራ እና በአፋር ክልል ወረራ ካደረገ በኋላ በመስህብ ስፍራዎች ላይ ከፍተኛ ውድመት በመከሰቱ የቱሪዝም መዳረሻ ልማቶችን በማስፋት የተሻለ የቱሪዝም መስህብ የመፍጠር ስራ እንዳይሰራ እንቅፋት መፍጠሩን ጠቁመዋል።

ከዚህ ባለፈም የመስህብ ስፍራዎቹ መደበኛ ይዞታቸውን ይዘው እንዳይቀጥሉ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ህልውናቸውን የማጥፋት ስራ እና ዘረፋ ተካሂዶባቸዋልም ነው ያሉት።

ይህንን ውድመት ለመታደግም ከፍተኛ የቅንጅት ስራ ይጠይቃል ብለዋል የቢሮ ሃላፊው፡፡

የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ ሰዓዳ ዑስማን በበኩላቸው ቱሪዝም በዋናነት ሰላምን እንደሚፈልግ ገልጸዋል።

ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ እንደ ሃገር በአማራና በአፋር ከፍተኛ ውድመት በመከሰቱ በጣም ማዘናቸውን ገልጸ ው በጦርነቱ ያሳየነውን አብሮነት የወደመውን መሰረተ ልማት በጋራ መልሰን በመገንባት አብሮነትን ማጠናከር እንደሚገባም አውስተዋል።

በኦሮሚያ ደረጃ አሸባሪው ሸኔ በሚንቀሳቀስባቸው አንዳንድ አካባቢዎች የጸጥታ ችግር በመፈጠሩ ጎብኚዎች እንደልባቸው ያለምንም ስጋት እንዳይንቀሳቀሱ አድርጓል ያሉት የቢሮ ሃላፊዋ፥ ጠላቶቻችን ሙሉ በሙሉ ደምስሰን በቅርቡ ወደ ልማታዊ ስራዎቻችን እንመለሳለንም ብለዋል፡፡

የክልሉ መንግስትም በጦርነቱ የወደሙ አካባቢዎችን ወደነበሩበት ለመመለስ በጦርነቱ ጊዜ እንዳደረገው ሁሉ አሁንም በቀዳሚነት የማቋቋም ስራውን ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አስረድተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የ”ወደ ሃገር ቤት ጥሪ” ተከትሎ ወደ ሃገርቤት የሚገቡ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች ሲገቡ አቀባበል ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም የሁለቱም ክልሎች ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊዎች ገልጸዋል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.