የሀገር ውስጥ ዜና

በ”ታላቁ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ” መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እንግዶችን ለመቀበል የተቋቋመው ኮሚቴ ዝግጅቱን አጠናቋል – አቶ ደመቀ መኮንን

By Feven Bishaw

December 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በ”ታላቁ ወደ ሀገር ቤት ጥሪ” መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እንግዶችን ለመቀበል የተቋቋመው ብሔራዊ ኮሚቴ ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አንድ ሚሊየን ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ ጥሪ ማቅረባቸው የሚታወስ ነው።