Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የሰዓት እላፊ ገደብ ላይ ማሻሻያ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል የሰዓት እላፊ ገደብ ላይ ማሻሻያ መደረጉን የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታወቀ፡፡
 
የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃለፊ አቶ ግዛቸው ሙሉነህ በሰጡት መግለጫ፥ የክልሉ የፀጥታ ኮማንድ ፖስት በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ውይይት ካደረገ በኋላ በተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ ማሻሻያ አድርጓል፡፡
 
ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ጠዋት 12 ሰዓት የተጣለው የሰዓት እላፊ ገደብ በክልሉ ያለው የጸጥታ ሁኔታ እየተሻሻለ በመምጣቱ የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴዎች እንዳይዳከሙና በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ዳያስፖራዎችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ ማሻሻያ ተደርጓል ነው ያሉት፡፡
በዚህም መሰረት የሰዓት እላፊ ገደቡ ከምሽቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋት 11 ሰዓት ድረስ ማሻሻያ መደረጉን አሚኮ ዘግቧል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.