Fana: At a Speed of Life!

የኢፌድሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን በምእራብ ዕዝ ተከበረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ)  8ኛው የኢፌድሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ቀን በምእራብ ዕዝ ተከበረ።

ቀኑ የተከበረው የምዕራብ ዕዝ መከላከያ ሰራዊት በደቡብ ጎንደር ዞን ጉና በጌምድር ወረዳ ያስገነባው የበጌምድር 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጨርሶ በማስመረቅና ለማህበረሰቡ በማስረከብ ስነ ስርዓት ነው።

የመከላከያ ሠራዊት በዓል “የሀገራችን ልዓላዊነትና የህዝብችንን ሠላም በፅናት እንጠብቃለን” በሚል መሪ ቃል የምዕራብ ዕዝ ቀኑን ያከበረው።

የምዕራብ ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከወር ደሞዛቸው በማዋጣት ባሰባሰቡት ገንዘብም ትምህርት ቤቱ መገንባቱን ዛሬ በርክክቡ ላይ ተገልጿል።

በ22 ሚሊየን ብር ወጪ በ10 ወራት ውስጥ ተገንብቶ የተጠናቀቀው ትምህርት ቤቱ ስምንት ህንፃዎች ያሉት ሲሆን፥ 40 የመማሪያ ክፍሎችን ይዘዋል።

 

በናትናኤል ጥጋቡ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.