የሀገር ውስጥ ዜና

የጀርመን ኤምባሲ ከ1942 ጀምሮ የታተሙ ሙሉ የነጋሪት ጋዜጣ ስብስብን ለቤተ መዛግብት እና ቤተ መጽሐፍት አስረከበ

By Alemayehu Geremew

December 23, 2021

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የጀርመን ኤምባሲ ከ1942 ጀምሮ የታተሙ ሙሉ የነጋሪት ጋዜጣ ስብስብን ለብሔራዊ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መጽሐፍት ባለፈው ሳምንት አስረክቧል፡፡

የጀርመን ኤምባሲ በአዲስ አበባ ለረጅም ጊዜያት በመዝገብ ቤት ውስጥ በጥንቃቄ ተይዘው የቆዩትን ከ1942 ጀምሮ የታተሙ ሙሉ የነጋሪት ጋዜጣ ለኢትዮጵያ ቤተ -መዛግብት እና ቤተ -መጽሐፍት ባለፈው ሳምንት ማስረከቡ ተገልጿል፡፡

የቤተ መዛግብቱ ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል ጠና በጀርመን ኤምባሲ በመገኘት የጀርመን አምባሳደር በኢትዮጵያ ከሆኑት አምባሳደር ስቴፈን አውር ነጋሪት ጋዜጦቹን ተረክበዋል።

የጀርመን ኤምባሲ የኢትዮጵያን ቅርሶች ጠብቆ ለማቆየት በሚደረገው ስራ የሁልጊዜ አጋርነቱን መግለጹን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ መላክታል፡፡