Fana: At a Speed of Life!

በቦረና ዞን ባለፉት 2 ሳምንታት 453 የህወሓት እና ሸኔ ሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ባለፉት ሁለት ሳምንታት 453 የህወሓት እና ሸኔ ሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
 
የቦረና ዞን አስተዳዳሪ አቶ ጃርሶ ቦሩ እንደገለጹት÷የሽብር ቡድኖቹ አባላት በቁጥጥር ስር የዋሉት ፖሊስ ከማህበረሰቡ ጋር ባካሄደው የተቀናጀ ዘመቻ ነው፡፡
 
በቁጥጥር ስር ከዋሉት ውስጥም 123ቱ የሸኔ አባላት ሲሆኑ÷330ዎቹ ደግሞ የአሸባሪው ህወሓት አባላት ናቸው፡፡
በዛሬው ዕለትም በዲሬ ወረዳ ተጨማሪ 26 የሸኔ ሽብር ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስተዳዳሪው ተናግረዋል፡፡
 
አቶ ጃርሶ የሽብር ቡድኖችን አባላት በቁጥጥር ስር የማዋሉ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መግለጻቸውንም ከዞኑ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.