Fana: At a Speed of Life!

ባሳለፍነው ሳምንት በከፍተኛ የመንግስት አመራሮች የተደረጉ የዲፕሎማሲያዊ ጉዞዎች ስኬታማ ነበሩ – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሳለፍነው ሳምንት በከፍተኛ የመንግስት አመራሮች የተደረጉ የዲፕሎማሲያዊ ጉዞዎች ስኬታማ እንደነበሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡
 
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ፥ ባሳለፍነው ሳምንት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሶስት የአፍሪካ ሀገራት ማለትም በኮትዲቯር፣ አንጎላ እና ጋቦን የስራ ጉብኝት ማድርጋቸውን አስታውሰዋል፡፡
 
በዚህም ከሀገራቱ ፕሬዚዳንቶች ጋር ባደረጉት ውይይት በኢትዮጰያ ወቅታዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸውን አስረድተዋል፡፡
 
በምክክሩም የሶስቱ ሀገራት መሪዎች ለኢትዮጵያ ድጋፍ እንደሚሰጡ አረጋግጠዋል ነው ያሉት፡፡
 
ከአፍሪካ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ጋር በነበራቸው ቆይታም ባንኩ ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጡን ነው የተናገሩት፡፡
 
በተመሳሳይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በቱርክ ባደረጉት ጉብኝት ከፕሬዚዳንት ረጅብ ጣይብ ኤርዶኻን ጋር ቆይታ ያደረጉ ሲሆን፥ሀገራቱ አሁን ያላቸውን የግንኙነት ደረጃ ከፍ ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ማድረጋቸውን ጠቁመዋል ፡፡
 
የአፍሪካ ሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት አባላት ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ምክክር ማድረጋቸውንም አምባሳደር ዲና በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡
 
በዚህም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በአፍሪካ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ ቀዳሚ ተግባር መሆን እንዳለበት ማብራሪያ ሰጥተዋል ነው ያሉት፡፡
 
አፍሪካ ያሉባትን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትም በሴቶች እና ወጣቶች ላይ ማተኮር እንዳለባት አቶ ደመቀ መግለጻቸውን በመግለጫው ተመላክቷል።
 
የምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው፥ የህገ ወጥ ገንዘብ እና የጦር ማሳሪያ ዝውውር፣ የውጭ ሀገራት ጫና አንዲሁም የአየር ንብርት ለውጥ በአፍሪካ እንደ ችግር እንደሚነሱ ተናግረዋል፡፡
 
በሌላ በኩል ዳያስፖራው ወደ አገር ቤት እንዲመጣ የተደረገው ጥሪ አንድነትን ለማጠናከር፣ የውጭ ሃይሎችን ጫና ለመቋቋም እና የመልሶ ማቋቋም ስራውን ለማገዝ ዓላማ እንዳለው ተነስቷል፡፡
 
ለዚህም አስፈላጊው ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን ነው ቃል አቀባዩ የገለጹት፡፡
 
በተለይም የገና እና የጥምቀት በዓላት በድምቀት በሚከበሩበት ላሊበላ እና ጎንደር ዝግጅቶች እየተደረጉ መሆኑን አምባሳደር ዲና ጠቁመዋል፡፡
 
በሜሮን ሙሉጌታ
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.