Fana: At a Speed of Life!

ወደ ኢትዮጵያ የሚላከውን ገንዘብ ለማሳደግ ቀልጣፋ የፋይናንስ ሥርዓት ያስፈልጋል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው ወደ አገር ቤት የሚልከውን ገንዘብ ለማሳደግ መንግሥት ቀልጣፋ የፋይናንስ ሥርዓት መዘርጋት ይኖርበታል ሲሉ በደቡብ አፍሪካ የሱዋኔ ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ምሁሩ ፕሮፌሰር ሙላቱ ፍቃዱ ተናገሩ።
ዳያስፖራው ወደ አገር ቤት የሚልከው ገንዘብ ሕጋዊ ሥርዓትን መከተል እንዳለበት ያሳሰቡት ፕሮፌሰር ሙላቱ፥ ከውጭ የሚላከው ገንዘብ የአገሪቷን ኢኮኖሚ ለመደገፍ ጉልህ ሚና ያለው በመሆኑ ዳያስፖራው ይህን በመገንዘብ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
በእስያ የሚገኙ አገራት ከአጠቃላይ ምርታቸው ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ከውጭ አገር በሚገባ ገንዘብ እንደሚያገኙ ለማሳያነት ጠቁመው፥ በዚህ መልኩ የሚገኝ ገቢ ለኢትዮጵያም እንደ ተጨማሪ የኃብት ማሰባሰቢያ ተደርጎ መወሰድ አለበት፤ መንግሥትም ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራበት ይገባል ብለዋል።
በተለይም ዳያስፖራው ገንዘቡን ያለምንም ችግርና ቅድመ ሁኔታ ወደ አገር ቤት እንዲልክ ለማድረግ ቀልጣፋ የገንዘብ ፍሰት መኖር እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
በሌላ በኩል የአገሪቷን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማጎልበት በቀጣናው ከሚገኙ ጎረቤት አገራት ጋር ሁለንተናዊ ትስስር ማጠናከር እንደሚገባም ጠቁመዋል።
በማንኛውም የልማትና የእድገት እንቅስቃሴዎች ከአፍሪካ በተለይም ከጎረቤት አገራት ጋር ያለውን ትብብር ማጠናከር ያስፈልጋልም ብለዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ዳያስፖራው ባለፉት ሶስት ዓመታት በአማካይ 3 ቢሊየን ዶላር በየዓመቱ ወደ አገር ውስጥ መላኩን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.