Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የንግድ ፍቃድ እድሳት በተያዘው ወር ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐምሌ ወር የተጀመረው የንግድ ፍቃድ እድሳት በተያዘው ወር እንደሚጠናቀቅ እና ወደ ቅጣት እንደሚገባ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የንግድ ፍቃድ እድሳት እና አገልግሎት አሰጣጡን በቂርቆስ፣ አራዳ እና አዲስ ከተማ ክፍለ ከተሞች ተዘዋውሮ ቅኝት አድርጓል።

ከንግድ ፍቃድ እድሳት ጋር የተያያዙ ጉዳዮች አገልግሎት አሰጣጥ መሻሻል ማሳየቱን የገለጹት አስተያየት ሰጭዎቹ÷ ጊዜ እና ድካምን እንደቀነሰላቸውም አስረድተዋል፡፡

የክፍለ ከተሞቹ የስራ ሀላፊዎች እንደገለጹት የንግዱ ማህበረሰብ የንግድ ፈቃዱን ለማደስ ቀናት ቢቀሩትም “ጊዜ አለ” በማለት መዘናጋት እና ቸልተኝነት እየታየበት ነው ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ምክትል ሀላፊ መስፍን አሰፋ ÷ የንግዱ ማህበረሰብ ተቋማትም ሆኑ ግለሰቦች ንግድ ፍቃዳቸውን እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲያድሱ አሳስበው÷ ከጥር ወር ጀምረው የንግድ ፍቃዳቸውን ባላደሱ አካላት ላይ ቅጣት እንደሚጀመርም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

እስከ ወረዳ ባሉ መዋቅሮች አሰራሮችን ዘመናዊ በማድረግ የንግዱ ማህበረሰብ ባለበት ቦታ ሆኖ አገልግሎቱን እንዲያገኝ መደረጉንም ተናግረዋል፡፡

በሲሳይ ጌትነት

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.