Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ከ6 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት አውድሟል

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14 ፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ከ6 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማውደሙን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ገለጹ፡፡
 
አሻባሪው ህወሓት በወልዲያ እና አካባቢው በወረራ በቆየባቸው ወራት ዩኒቨርሲቲውን ጨምሮ በርካታ የህዝብና የግለሰብ ንብረቶችን ዘርፏል፤ ያልቻለውን አውድሟል ።
 
የወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር አበበ ግርማ÷ዩኒቨርሲቲው በአሻባሪው ህወሓት ከ6 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ማጣቱን ተናግረዋል።
 
አሸባሪው ህወሃት የዩኒቨርሲቲውን ቢሮዎች ክፉኛ ሰባብሯል፣ የላብራቶሪ እቃዎች እና ኮምፒተሮች፣ የዩኒቨርሲቲው ገስት ሀውስ፣ አይሲቲ ክፍሎች፣ ላይብረሪና ኢ-ላይብራሪ ህንፃውና በውስጡ የነበሩ ንብረቶች ዘረፋና ከፍተኛ ውድመት ተፈፅሞባቸዋል ብለዋል።
 
የዩኒቨርሲቲውን መሰረታዊ መማር ማስተማር ለማስጀመር የሚያስችል መርሃ ግብር ተቀርጾ እየተሰራ መሆኑን ፕሬዚደንቱ ጠቅሰዋል።
 
የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያውያን የሚማሩባቸውን፣ የሚታከሙባቸውን እንዲሁም የተለያዩ አገልግሎቶች የሚያገኙባቸውንና ሰርተው ኑሯቸውን የሚደጉሙባቸውን ፋብሪካዎች ጭምር በመዝረፍና በማውደም የክፋት ጥጉን አሳይቷል ብለዋል።
 
ቀደም ሲል በዩኒቨርሲቲው በመምህርነት የሰሩና የተማሩ ጭምር የአሸባሪው ቡድን አባል በመሆን “የበሉበትን ወጭት ሰባሪ” ሆነው መገኘታቸውን አረጋግጠናል ብለዋል ዶክተር አበበ።
 
በዩኒቨርሲቲው ላይ የተፈፀመው ዘረፋና ውድመት የከፋ ቢሆንም የአጭር፣ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ እቅድ በማውጣት ወደ ነበረበት ለመመለስ ጥረት ይደረጋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.