Fana: At a Speed of Life!

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በጦርነቱ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች እና ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት የ15 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚ ሽፈራው ሰለሞን፥ በሽብር ቡድኑ ጥቃት ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው በሸዋሮቢት እና ደብረ ብርሃን ከተሞች ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች እንዲሁም ለሰራዊት አባላቱ የሚውል የአልባሳት፣ የንፅህና መጠበቂያ እና የምግብ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።
በሁለቱ ከተሞች የተደረጉት ድጋፎች በአጠቃላይ 15 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ቁሳቁስ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከዚህ ቀደም በኮምቦልቻ፣ ደሴ እና ሰመራ ያደረገውን ድጋፍ ጨምሮ እስካሁን ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ሃብት ለህልውና ዘመቻው አስተዋፅኦ አድርጓል ብለዋል፡፡
አሸባሪው ህወሓት ያደረሰው ውድመት ከፍተኛ በመሆኑ፥ ድጋፉ ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚው የተናገሩት።
በሸዋሮቢት ድጋፉን የተረከቡት የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ዘነበ ተክሌ፥ ኮርፖሬሽኑ ላደረገው ድጋፍ አመስግነው÷ ድጋፉን በተገቢው መንገድ እናከፋፍላለን ብለዋል፡፡
ሌሎች ተቋማትም ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚያደርጉትን እገዛ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
የተደረገውን ድጋፍ የፀጥታ ችግሩ ተከስቶባቸው በነበሩ አካባቢዎች በፍጥነት ይደርሳል ተብሏል፡፡
በሰላም አሰፋ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.