Fana: At a Speed of Life!

ኦሚክሮን ኢትዮጵያ ውስጥ መከሰት አለመከሰቱን ለማረጋገጥ ምርምር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 14 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦሚክሮን የተሰኘው የኮቪድ-19 አዲሱ ዝርያ ኢትዮጵያ ውስጥ መከሰት አለመከሰቱን ለማረጋገጥ ናሙና በመውሰድ ምርምር እየተካሄደ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሥርጭት ምጣኔና የወረርሽኙን ሁኔታ በሚመለከት የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 የሥርጭትና የሞት ምጣኔ እየጨመረ በመምጣቱ የማህበረሰቡ የጤና ስጋት ከመሆን አልፎ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በአገሪቱ እስከ ትናንት ድረስ ከ4 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ ሰዎች የኮቪድ-19 ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ 382 ሺህ ሰዎች ላይ ቫይረሱ መገኘቱን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመለክታል።

ባለፈው ህዳር ወር የተከሰተው አዲሱ አሚክሮን ኮቪድ19 በሁለት ወራት ውስጥ በ106 ሀገራት መገኘቱን አብራርተዋል።

ሚኒስትሯ ኦሚክሮን ቫይረስ በፍጥነት የሚዛመት ከመሆኑ ባሻገር ከዚህ ቀደም በኮቪድ-19 ተይዘው የነበሩ ሰዎችን ጭምር በፍጥነት የሚያጠቃ ነው ብለዋል።

በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ከሁለት ሳምንት ወዲህ የኮቪድ-19 ምጣኔ የጨመረ ሲሆን ከነበረበት ሦስት በመቶ ወደ 28 በመቶ አድጓል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.