የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ በአንድ ቀን ብቻ በኮሮና ቫይረስ 3 ሺህ 793 ሰዎች ተያዙ

By Meseret Awoke

December 23, 2021

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በኮሮና ቫይረስ 3 ሺህ 793 ሰዎች ተይዘዋል፡፡

የጤና ሚኒስቴር በዕለታዊ ሪፖርቱ እንዳስታወቀው ÷ 13ሺህ 147 ሰዎች ተመርምረው 3ሺህ 793 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

አምስት ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ህይወታቸው ማለፉም ነው የተገለጸው፡፡

በአንጻሩ 89 ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸው ተመላክቷል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ! ወደ ግንባር ይዝመቱ! መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!