Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ደንቢያ ወረዳ አንዲት እናት አራት ህፃናትን ተገላገለች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ ደንቢያ ወረዳ አንዲት እናት አራት ህፃናትን በሰላም ተገላገለች።

በደንቢያ የመጀመርያ ደረጃ ሆስፒታል በዛሬው እለት ከጠዋቱ 2 ስዓት እናት አራት ወንድ ጨቅላ ህፃናትን በሰላም መገላገሏ ነው የተነገረው።

አሁን ላይ ህፃናቱ እናና እናትየዋ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አዘዘው አዲስ መናገራቸውን ከደንቢያ ወረዳ ኮሙኒኬሽ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.